EthiopiaNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ የግድያ ሙከራ ተወጥኖባቸው ነበር የሚለው መረጃ ላይ እምነት እንደሌለው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አስታወቀ።

ሲአይኤን ጠቅሶ ዋሽንግተን ፖስት እንደዘገበው የግድያ ሙከራው መረጃ ከእስራኤል መረጃ ድርጅት የመጣና የአሜሪካ ደህንነት ሰዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያለመ ነው።

የመረጃው እውነተኛነት ላይ ጥርጣሬ ቢኖርም የፕሬዝዳንቱ ጠባቂዎች መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ወስደዋል።

ትራምፕ ከቱርኩ ስጋት በኋላ አውሮፕላን እየቀያየሩ ወደ አገራቸው መመለሳቸው የተዘገበው ባለፈው ሰኞ ነበር።