የፍልስጤሙ ሀማስ ትጥቅ ካልፈታ የጋዛ መልሶ ግንባታ የሚባል እንደማይኖር አሜሪካ አስታወቀች።
የፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰላም መልዕክተኛ ያሬድ ኩሽነር እንደሚሉት ሀማስ ጋዛን ከእንግዲህ የሚቆጣጠር ከሆነ ወይም በግዛቷ የፍንዳታ ድምፅ ከተሰማባት በዚያች ግዛት መልሶ ግንባታ የሚባል ነገር የለም።
ያሬድ ኩሽነር ይሄን ያሉት በቅድሚያ ከሀማስ መሪዎች በመቀጠል ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ሰሞኑን ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ነው።
ኩሽነር ብዙም ያልተመደበውን የፊት ለፊት ንግግር ከሀማስ ጋር ያደረጉት በካይሮ ነበር። ኩሽነር እንደሚሉት ሀማስ የትራምፕን የሰላም ሀሳብ በመቀበል ሙሉ ለሙሉ ትጥቅ እፈታለሁ ብሏል።
ኩሽነር ለፎክስ ኒውስ ሲናገሩ የሀማስ ቃል ወደ ተግባር መለወጡ በጊዜ ሂደት የሚታይ ይሆናል ነው ያሉት።
