የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ለክልሉ የ2019 በጀት ዓመት የሥራ ማስፈጸሚያ የሚውል ከ18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ማጽደቁ ተገለጸ።
በክልሉ ወጪዎችን በራስ የገቢ ምንጭ ለመሸፈን አበረታች ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ለ2019 በጀት ዓመት ከተያዘው አጠቃላይ በጀት ውስጥ ከ11 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነውን በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ ለመሸፈን መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡
ቀሪው 7 ቢሊየን ብር ደግሞ ከፌደራል መንግስት በድጎማ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው።
በክልሉ የሚገኙ የፋይናንስ አቅሞችን በመጠቀም ገቢን ለማሳደግ የተጀመሩ አበረታች ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ የምክር ቤቱ አባላት አስገንዝበው በበጀት ዓመቱ የተያዘው በጀት የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲውል በየደረጃው ክትትል ማድረግ ይጠበቃልም ማለታቸው ተገልጿል።
