ፕሬዝዳንቱ ይሄን ያሉት ሰሞኑን ከኢራን ጋር የሚደረግ ድርድር የለም፤ ይችን ሀገር የምናንበረክከው እጅግ ፈታኝ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ማዕቀቦችን በመጣል ነው ካሉ በኋላ ነው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ተከታታይ የአየር ድብደባ አቋማቸውን የቀየሩት የአሜሪካ አልሞ መቺም ሆነ የመከላከያ ሚሳኤሎች ክምችት በመመናመኑ እንደሆነ ሲነገር ሰንብቷል።
ትራምፕ ኢራንን በማዕቀብ አንበረክካለሁ ቢሉም አገሪቱ ለአስርት ዓመታት በከባድ ማዕቀብ ስር በመቆየቷ በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ ባለሙያዎች በስፋት እየተናገሩ ነው።
