EthiopiaNews

የአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ አፍሪካ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ የሚስፈልጓትን 75 ሺህ አዳዲስ የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ለማብቃት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

ኩባንያው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው አራተኛው የስልጠና መርሃ-ግብር ላይ 28 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በአቪዬሽን ሙያ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን የስድስት ሳምንታት ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ መቻሉንም ነው የገለጸው፡፡

ስልጠናው የዲጂታል ክህሎቶችን እና የተግባር ልምምዶችን ያካተተ መሆኑን የገለጸው ኩባንያው በዚሁ መርሃ ግብር ባለፉት ጥቂት አመታት ከ100 በላይ የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ማብቃት መቻሉንም ገልጿል፡፡