EthiopiaNews

የጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የዲጂታል ጤና ኢንተርፕራይዝ አርክቴክቸር በምህፃሩ (ዲኤችኢኤኢቲ) የተሰኘ አዲስ የአሰራር ማዕቀፍ ይፋ አደረገ።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሰሀረላ አብዱላሂ አዲሱን የአሰራር ማዕቀፍ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ዲጂታል ጤና ተቋማዊ፣ ተቀናጅቶ የሚሰራና ሰው-ተኮር የጤና ሥርዓት ለመገንባት ወሳኝ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ ዲጂታል ጤና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን፣ ተቋማትን፣ አሠራሮችን፣ የሰው ኃይልን፣ መረጃንና ቴክኖሎጂን በአንድ የጋራ ስነ ምህዳር ማስተሳሰር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ዲኤች ኢኤ ኢቲ የተሰኘው አዲሱ የአሰራር ማዕቀፍ የቴክኖሎጂ ሰነድ ብቻ ሳይሆን፣ የዲጂታል ጤና አሠራሮች በቅንጅት እንዲሰሩ፣ መረጃ በቀላሉና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጋራ እና የተለያዩ ዲጂታል መፍትሔዎች በጋራ መመዘኛና አቀራረብ እንዲለሙ የሚያስችል ሀገራዊ አቅጣጫ መሆኑ ተገልጿል።

መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv