የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት 124 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።
ተቋሙ ይህንን የገለጸው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው፡፡
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሽብር ባልቻ ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን 124 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ሰብስቧል ነው ያሉት።
አክለውም በዓመቱ ከተገኘው ጠቅላላ ገቢ ውስጥ 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብሩ የተጣራ ትርፍ መሆኑን ተናግረው፤ በበጀት ዓመቱ 475 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ መሰብሰብ መቻሉንም ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅና ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መግባት እንዲሁም የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ወደ ኦፕሬሽን በመግባታቸው የሀገሪቱ አጠቃላይ የኤሌክትሪካ ህይል የማመንጨት አቅም 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ደርሷል ብለዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የተቋሙን የገቢ አቅም ለማሳደግ የተጫወተው ሚና የላቀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
