EthiopiaNews

በጎፋ ዞን ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ጨቅላ ህጻናትን በሰላም መገላገሏ ተነገረ፡፡

እናቲቱና አራቱም ጨቅላ ህጻናት በአሁኑ ወቅት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡

የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ግላንደ ጊሎ እንደገለጹት በሆስፒታሉ ደረጃ ሁለትና ሦስት ህጻናትን በአንድ ጊዜ ማዋለድ የተለመደ ቢሆንም በአንድ ወሊድ አራት ህጻናትን በሰላም ማዋለድ መቻሉ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያ ነው ብለዋል።

ዶ/ር ግላንደ ጊሎ እናቲቱ ለተከታታይ አምስት ቀናት በቅርብ የሕክምና ክትትል ስር ቆይታ በኋላ አራቱንም ህጻናት በሰላም መገላገሏን ተናግረዋል።

ዘገባው የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ነው።