EthiopiaNews

የአፍሪካ ሕብረት የራሱን አህጉራዊ የብድር ደረጃ ሰጪ ኤጀንሲ ሊያስጀምር መሆኑን ገለጸ።

በመጪው ጥቅምት በሞሪሸስ ስራ ይጀምራል የተባለው ይህ ኤጀንሲ በአህጉሪቱ ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የብድር ወለድ ጫና ለመቋቋም ያስችላል የሚል እምነት ተጥሎበታል፡፡

ምዕራባቸውያን የደረጃ ሰጪ ኤጀንሲዎች የአፍሪካ ሀገራት የብድር ስጋት በትክክል እንደማይገመግሙ በተዳጋጋሚ ጊዜ አፍሪካውያን መሪዎች ቅሬታ ሲያነሱ የቆዩ ሲሆን ይህ ኤጀንሲ ይህንኑ የሀገራት የብድር ስጋት በትክክል ለመገመትም ያስችላል ነው የተባለው፡፡

ይህ ተቋም አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደማጭነት ካላቸው እንደ ፊች፣ ሙዲስ እና ኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ካሉ ተቋማት የተለየ አማራጭ እንዲያገኙ ያስችላልም መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል፡