የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ አገራት የሩሲያን የአየር ክልል ለበረራ እንዳይጠቀሙ አስጠነቀቁ።
ዜሌንስኪ ማስጠንቀቂያውን የሰጡት አገራቸው በሩሲያ ሰማይ ላይ የድሮን ጥቃትን በማጠናከሯ መሆኑን ገልፀዋል።
ዜሌንስኪ እያንዳንዱ አየር መንገድ፣ እያንዳንዱ የአውሮፕላን ደህንነት ዋስትና ሰጭና የሩሲያ አየር ማረፊያዎች ከእንግዲህ ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ መሆኑን ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።
በርካታ ምዕራባዊያን አየር መንገዶች በጦርነቱ ምክንያት ወደ ሩሲያ በረራ ያቆሙ ሲሆን እንደ ቻይና ያሉ አገራት አየር መንገዶች ወደ ሩሲያ እንደሚበሩ የቢቢሲ ዘገባ አስታውቋል።
ለዚሁ ማስጠንቀቂያ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሰጡት ምላሽ የዜሌንስኪ ንግግር ከመንግስታዊ አሸባሪነት ተነጥሎ አይታይም ብለዋል።
