ጀርመን በቅርቡ በሌፕዚግ አየር ማረፊያ ለደረሰው የድሮን ጥቃት ሩሲያን ተጠያቂ አደረገች።
ልክ የዛሬ ወር ግድም በምስራቅ ጀርመን ከተማ የሌፕዚግ አየር ማረፊያ ወደ ዩክሬን ጭነት ከያዙ አውሮፕላኖች አቅራቢያ አንድ ፈንጂ የጫነ ድሮን ተገኝቷል።
ይህ ድሮን ጉዳት ያላደረሰው የፈንጂ ማቀጣጠያው ባለመስራቱ ሲሆን ሁለተኛ ድሮን ደግሞ ከአንድ የዩክሬን የጭነት አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ ነበር። ከአስር ቀናት በኋላም ሌላ ሦስተኛ ድሮን በአቅራቢያው ወድቆ ተገኝቷል።
የጀርመኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪዲት የድሮን ጥቃቱ ሩሲያ በድጋሚ ጀርመንን ኢላማ ማድረጓን ማሳያ ነው ብለዋል።
የሩሲያ መንግስት በፊናው ከጀርመን የቀረበበትን ክስ ፈፅሞ ትርጉም የሌለው ነው ብሏል።
