EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እቃ ጫኝ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ለመግዛት መቃረቡ ተነገረ።

ሮይተርስ የዜና ወኪል የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 እቃ ጫኝ አውሮፕላኖችን ከቦይንግ ኩባንያ ለመግዛት ጫፍ እንደደረሰ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

አየር መንገድ ሊገዛ ካላቸው አውሮፕላኖች ውስጥ ሁለቱ የቦይንግ 777 ኤፍ ሞዴል እንዳለበት ምንጮች ነገሩኝ ሲል ሮይተርስ አስነብቧል።

ይሁን እንጂ በዚሁ ግዥ ዙሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ የቦይንግ ኩባንያ ምንም ያሉት ነገር እንደሌለ በዘገባው ተጠቅሷል።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ያለፈው ሰኔ ወር አየር መንገዱ በሚገዛቸው 25 አነስተኛ አውሮፕላኖች ዙሪያ በ3 ወራት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል ማለታቸው ይታወሳል።