ጀርመን በፈረንጆቹ 2026 የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ለእስራኤል የሚደረግና 930 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የጦር መሣሪያ መሸጧ ተገለጸ።
“ዴር ስፒገል” የተሰኘው የጀርመን ጋዜጣ የመንግሥትን መረጃ ጠቅሶ እንደዘገበው፤የተፈቀደው የጦር መሣሪያ መጠን ባለፈው ዓመት ከተፈቀደው አጠቃላይ መጠን በአራት እጥፍ ብልጫ ያለው ነው ብሏል።
ይህ የጦር መሣሪያ ሽያጭ የጨመረው በርሊን ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር ላይ በእስራኤል የጋዛ ወረራ ምክንያት ጥላው የነበረውን ጊዜያዊ ማዕቀብ በማንሳቷ ምክንያት እንደሆነ ነው የተገለጸው።
በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብራቸውን እያሰፉ የሚገኙ ሲሆን፣ የጀርመን ባህር ኃይል በቅርቡ እስከ 500 ኪሎ ሜትር መተኮስ የሚችል የእስራኤል ባሊስቲክ ሚሳይልን በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ በስኬት መሞከሩ ታውቋል።
በሌላ በኩል ይህ ውሳኔ በጀርመን የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢያስነሳም የሃገሪቱ መንግሥት ለእስራኤል የሚያደርገውን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ አሁንም አጠናክሮ መቀጠሉ ተመልክቷል።
