EthiopiaNews

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞቹ ቁጥር ከ15 ሚሊዮን በላይ መድረሱን አስታወቀ።

ኩባንያው ይሄን ያለው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ከገባ አምስተኛ አመት የሞላው መሆኑን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

ኩባንያው የስራ ፈቃዱን ተቀብሎ ወደ ስራ ከገባ በኋላም ከ3,500 በላይ የኔትወርክ ሳይቶችን መገንባቱን አስታውቋል።

ሳፋሪኮም በአሁኑ ወቅት ኔትወርኩ በኢትዮጵያ 60 በመቶ ያህል ሰዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልፆ ሁሉም የኔትወርክ ሳይቶቹ የ4G (የአራተኛው ትውልድ ) የሚያስጠቅሙ እና ለ5G (ለአምስተኛው ትውልድ) ዝግጁ እንደሆኑ ይፋ አድርጓል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በተለይም በገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል ከፍተኛ ጥራት ያለው የቴሌኮም ግንኙነት ማዳረስ መቻሉን ገልጿል።መረጃው ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተገኘ ነው።