EthiopiaNews

ለመጪው የ2019 ዘመን መለወጫ በዓል በአዲስ አበባና አካባቢዋ ከ4 ሺህ 500 በላይ የቁም እንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ለመጪው በዓል ያደረገውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የአገልግሎት ፈላጊው ቁጥር ከታቀደው በላይ ከፍ ቢልም ለመጣው ተገልጋይ በሙሉ አገልግሎት የመስጠት አቅም እንዳለው ነው የገለጸው፡፡

በመሆኑም ማንኛውም የከተማዋ ነዋሪ ጥራትና ደህነንቱ በተጠበቀ መልኩ በግና ፍየልን በ300 ብር፣ እንዲሁም በሬን ደግሞ በ2ሺ አንድ መቶ ብር በቄራ ድርጅቶች የእርድ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ተጠቁሟል።