EthiopiaNews

በቅርቡ የኤየር ኢንዲያ ስራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሪ ተወልደ ገብረ ማርያም ኤየር ኢንዲያ አየር መንገድን ታላቅ ለማድረግ ቃል ገቡ።

አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ይሄን ያሉት የኤየር ኢንዲያ ስራ አስፈጻሚ ሆነው ስራ በጀመሩበት ጊዜ ባደረጉት ንግግር ነው።

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሪ ተወልደ የኤር ኤንዲያ ሰራተኞች አየር መንገዱ ውጤታማ እንዲሆን እንዲተባበሩ ሲሉ በይፋ ጠይቀዋል።

የኤየር ኢንዲያ ሊቀመንበር ኤን ቻንድራሴካራን በቀጣይ የአየር መንገዱ ትኩረት የበረራ ደህንነት ማረጋገጥ እና የደንበኞች መተማመንን ማግኘት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ36 አመታት እንዲሁም በስራ አሰፈፃሚነት ለ11 አመታት ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገብረማርያም አየር መንገዱ እንዲያድግ የጎላ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።ዘገባው የህንዱ ፒቲአይ የዜና አገልግሎት ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv