የጃዚራ አየር መንገድ ከኩዌት አዲስ አበባ የቀጥታ በረራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
አየር መንገዱ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰይድ ጅብሪል እና የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በረራውን በይፋ አስጀምሯል።
የጃዚራ አየር መንገድ ከኩዌት አዲስ አበባ በሳምንት 3 ጊዜ በረራ እንዳለው ተገልጿል።
የአየር መንገዱ በረራ ስራ መጀመር በኩዌት የሚኖሩ ከ70ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
