በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 861 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 10 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 313 ወንዶች እና 485 ሴት እንዲሁም 63 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል አንድ መቶ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል ያለው ሚኒስቴሩ መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ101 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን ገልጿል።