EthiopiaNews

የአፍሪካ ቁጥር አንድ ባለሀብት የሆኑት ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ በታሪክ ትልቁ የተባለውን እና እስከ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ያለመውን የነዳጅ ማጣሪያ አክሲዮን ሽያጭ ይፋ አድርገዋል።

የህዝብ አክሲዮን ሽያጭ በተሰኘው በዚህ መርሃ ግብር ተራ ናይጄሪያውያን በትንሹ በ4 ዶላር አነስተኛ ክፍያ የአክሲዮን ባለቤት መሆን የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩ ተገልጿል።

በ20 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ይህ የነዳጅ ማጣሪያ፣ ናይጄሪያን ከነዳጅ አስመጪነት ወደ ላኪነት በመቀየር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ እመርታ ማምጣት የቻለ ነውም ተብሏል።

አክሲዮኑ በሙሉ ከተሸጠ የዚሁ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ አጠቃላይ የገበያ እሴት ወደ 49 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ይላል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተነግሯል።

ቢሊየነሩ ዳንጎቴ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያውን አክሲዮን በአሜሪካ የገበያ ማዕከል ለማውጣት እና የተቀሩትን ኩባንያዎቹንም ለህዝብ ክፍት ለማድረግ እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።