EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የመጀመሪያ የሆነውን የአፍሪካ የውሃ ኮንፈረንስ ከፊታችን መስከረም 11 እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል።

አዘጋጅ ኮሚቴው ይህን የገለጸው ከኮንፈረንሱ የሚጠበቁ የውይይት ውጤቶችና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

መድረኩ በአፍሪካ የውሃ ደህንነትን ማጠናከርና የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

በኮንፍረንሱ የተለያዩ ባለሙያዎች ጥናታዊ ፅሁፍ የሚቀርብ ሲሆን የፓናል ውይይትና የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡.

ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኮንፍረንስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወከሉ ከፍተኛ አመራሮችንና ምሁራንን ጨምሮ ከ300 በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉበት ተጠቁሟል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv