በተጠባባቂነት በመመዝገብ በማህበር ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላቸው የ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች በኦንላየን እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
ጥሪውን ያቀረበው በ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው በመቆጠብ ላይ ካሉ ቤት ፈላጊዎች ውስጥ በማህበር ተደራጅተው በጋራ ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸውን ተመዝጋቢዎች በማህበር አደራጅቶ መሬት በማስረከብ በተለያዩ ሳይቶች ግንባታ እንዲጀምሩ ማድረጉን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ነው።
ቢሮው በማህበሩ ውስጥ አባላት በተለያዩ ምክንያት ሲጎድሉ ተጠባባቂዎችን መዝግቦ በማዘጋጀት ለሚጎድሉ አባላት ተተኪ አባላት እንደሚመደብ የገለጸ ሲሆን በመሆኑም በተጠባባቂነት በመመዝገብ በማህበር ተደራጅቶ ቤት ለመገንባት አቅም እና ፍላጎት ያላቸው የ2005 ዓ.ም የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ብቻ በተዘጋጀው ሲስተም ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን አሳውቋል።
የ2005 የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢ የሆነ እና እየቆጠበ የሚገኝ፣ ለቤት ግንባታ የሚውለውን 70 በመቶ ገንዘብ ማህበራቱ እያከናወኑ በሚገኙበት ዋጋ መሠረት ማዋጣት የሚችል እና ቀሪውን 30 በመቶ ቢሮው ባመቻቸው መሠረት ከባንክ ለመበደር ፈቃደኛ የሆነ ብቻ መመዝገብ የሚችል መሆኑን ነው ቢሮው የገለጸው።
ምዝገባው የሚደረገው ኦንላይን ብቻ በመሆኑ ቢሮ መምጣት አያስፈልግም ያለው ቢሮው ተመዝጋቢዎች የሞባይል ስልካቸውን ተጠቅመው መመዝገብ እንደሚችሉም ገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
