EthiopiaNews

በሀገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም በአንድ ወር ውስጥ ብቻ 15 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።

ኤሌክትሪክን በመላ ኢትዮጵያ ለማዳረስ ሲተገበር በቆየው በዚህ ፕሮግራም በአንድ ወር ውስጥ 15 የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የሃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የገለጸው አገልግሎቱ በዚህም በአጠቃላይ 5 ሺህ 435 አባዎራዎች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያለው፡፡

እነዚህን የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 48 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር መካከለኛ መሥመር መዘርጋቱንም ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡

መሥመሩን ደንበኞች ደጃፍ ለማድረስም 162 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መሥመር ዝርጋታ ሥራ የተከናወነ መሆኑን እንዲሁም 34 የተለያየ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮችም ጥቅም ላይ መዋላቸውንም አክሎ ገልጿል፡፡

የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ከሆኑት የገጠር ቀበሌዎችና መንደሮች ውስጥ ዘጠኙ ከግሪድና ስድስቱ በፀሐይ ኃይል አማራጭ ተደራሽ የሆኑ ናቸውም ብሏል፡፡