EthiopiaNews

የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሁመድ አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበትን የክልሉ ፖሊስ ሠራዊት አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ።

የሆስፒታሉ ግንባታና የሕክምና መሣሪያዎች ጨምሮ በድምሩ አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን 700 ሚሊዮን ብር ለግንባታው ፣ 300 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለሕክምና መሣሪያዎችና ለጤና አገልግሎቶችን ወጪ መደረጉ ተጠቁሟል።

በተለይ ለፖሊስ አባላትና ለቤተሰቦቻቸው የተገነባው ሆስፒታሉ ወደ 200 የሚጠጉ ክፍሎች ያሉትና ለከባድና ቀላል ቀዶ ጥገና አገልግሎት ዘጠኝ ክፍሎች ያካተተ፣በተጨማሪም 10 አልጋዎች ያሉት የከፍተኛ የጤና ክትትል ክፍል እንዳለውም ተጠቅሷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፋ ሙሁመድ በሆስፒታሉ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የሆስፒታሉ ግንባታ ለጸጥታ ኃይሎችና ለቤተሰቦቻቸው የጤና እንክብካቤን ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ ወሳኝ ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።መረጃው ከሶማሊ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።