የኦሮሚያ ክልል አዳዲስ ዞኖችን በማዋቀር አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ መመደቡን አስታወቀ።
የክልሉ መንግሥት በሥራ ላይ ባዋለው አዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በክልሉ ስድስት አዳዲስ ዞኖች አዋቅሯል።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት የሚመሩ አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ በጨፌ ኦሮሚያ ሹመት ሰጥቷል።
በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት የተቋቋሙት 6ቱ ዞኖች ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን፣ ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን፣ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን፣ የደቡብ ኦሮሚያ ዞን፣ ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን እና የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን ናቸው።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት እንዲመሩ በጨፌ ኦሮሚያ የተሰጡት አዳዲስ የሹመት ድልድሎች እንደሚከተለው ሆነዋል፦
• አቶ አብዱርራህማን አብደላ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ መስፍን መላኩ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር ረሻድ ከማል፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር መንግሥቱ በቀለ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ኢድሪስ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ሀጂ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ።
