EthiopiaNews

በአዲስ አበባ የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን በ77 ነጥብ 3 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ገልጿል፡፡

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን በሩብ ዓመቱ የሕዝብና የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ከማድረግ ባለፈ የተለያዩ የደንብ መተላለፎች እንዳይከሰቱ ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የደንብ መተላለፎችን በዘላቂነት ለመቀነስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተጠቆመ ሲሆን የተቋሙን አፈጻጸም ይበልጥ ለማሳደግ ለአመራሮችና ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በከተማዋም እየቀነሰ የመጣውን የደንብ ጥሰቶችን ይበልጥ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡