በአዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ካቢኔ ውስጥ ያልተካተቱ 11 የቀድሞ ሚኒስትሮች;-
- የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
-
የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል
-
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር አለሙ ስሜ
-
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
-
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ
-
የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ
-
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
-
የማዕድን ሚኒስትሩ አቶ ሃብታሙ ተገኝ
-
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶክተር ካሳሁን ጎፌ
-
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ
-
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ
በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ካልተካተቱ 11 የቀድሞ ሚኒስትሮች ውስጥ አቶ አህመድ ሽዴ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢትዮጵያ ኒውክለር ኃይል ዋና ኮሚሽነር እንዲሁም ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በአዲስ የሃላፊነት ቦታ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
