የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ኤርትራ ጦሯን በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ ጠየቁ።
ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ሞሃመድ ጋር ትናንት በተወያዩበት ጊዜ ነው።
የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ግዛት መያዙን የገለጹት ሚኒስትሩ በቀጠናው ሰላም እና ደህንነት ላይ የሚኖረውን አንድምታ ለምክትል ዋና ፀሐፊዋ በዝርዝር አስረድተዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት ለጉዳዩ ፈጣን እና ግልጽ ምላሽ እንዲሠጥ የጠየቁት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን የማስከበር መብቷ የተጠበቀ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
መረጃው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
