የመንግስት የጤና ተቋማት ሀገራዊ መስፈርቶችን አሟልተው በመገኘታቸው የብቃት ማረገገጫ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ አክሎም ለ1 ሺህ 253 መድሃኒት ቤቶች የፈቃድ እድሳት መስጠቱንና ለ25 የጤና ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ መስጠቱንም ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል 197 በሚደርሱ የምግብና ጤና ነክ እንዲሁም ጤና ተቋማት ላይ እርምጃ በመውሰድ ከ8 ሚሊዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተበላሹና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው የምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ነክ ምርቶችን ማስወገድ መቻሉን ገልጿል፡፡
ቢሮው በሩብ አመቱ ለ3 ሺህ 490 የጤና ባለሞያዎች የሙያ ብቃት እድሳት አገልግሎት እንደሰጠ እንዲሁም ለ2 ሺህ 340 የሚሆኑ የጤና ባለሞያዎች ደግሞ አዲስ የሙያ ፈቃድ አገልግሎት መስጠት መቻሉን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ያስታወቀው ከዚህ ቀደም ሲሰጥ የነበረውን የጤና ሙያ ፈቃድ እድሳትና ሌሎች ተግባራት ከሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በኩል እንደሚሰጥ ባስታወቀበት መድረክ ላይ ነው፡፡
