EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14 ነጥብ 6 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አስታወቀ።

አገልግሎቱ የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበትን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይህ የዋጋ ግሽበት በጥቅምት 2018 አ.ም ከነበረው 11 ነጥብ 6 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ ያሳየ ነው ብሏል።

ምግብ እና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ በ14 ነጥብ 1 በመቶ፣ አትክልት በ11 ነጥብ 1 በመቶ፣ ስጋ በ23 ነጥብ 8 በመቶ ወተት፣ የወተት ተዋፅኦች እና እንቁላል በ20 ነጥብ 1 በመቶ የጨመረ ሲሆን ፍራፍሬ 11 ነጥብ 1 በመቶ፣ ዘይት እና ቅቤ በ20 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የምግብ ምርቶች በ15 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ ማሳየታቸውም ተጠቁሟል፡፡

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 15 ነጥብ 4 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 17 ነጥብ 1 በመቶ፣ ኮሚኒኬሽን 9 ነጥብ 1 በመቶ፣ ምግብ ቤቶች እና ሆቴሎች 11 ነጥብ 1 በመቶ፣ ትምህርት 15 ነጥብ 5 በመቶ እና ጤና 10 ነጥብ 5 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል።

የመስከረም ወር 2019 አ.ም የዋጋ ግሽበት 14 ነጥብ 9 በመቶ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው።