የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአለም ባንክ የሚደገፈው የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም በንጹህ የመጠጥ ውሃ እና በሳኒቴሽን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ።
የውሃና ኢነርጂ ሚነስቴር ይሄን ያለው ከአለም ባንክ ተወካዮች በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
በጁሊያን ቪክተር የተመራ የዓለም ባንክ ተወካዮች ቡድን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፉን እንደሚያጠናክር ነው ያስታወቀው።
ጁሊያን ቪክተር በኢትዮጵያ መንግሥትና በልማት አጋሮች በጋራ የሚደገፈው የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም ከዓለም ባንክ ከተገኘው 300 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ ለማንቀሳቀስ ማስቻሉን ጠቁመዋል።
የአለም ባንክ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚሰራቸው የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም ከአንዳንድ ተግዳሮቶች በስተቀር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የባንኩ የቡድን መሪው ጁሊያን ቪክተር በፕሮግራሙ በንጹህ የመጠጥ ውሃ እና በሳኒቴሽን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልፀዋል።
መረጃው ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
