የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ማእዶት ብሮድካስቲንግ አገልግሎት በድጋሚ የስያሜ ማሻሻያ በማድረግ ” ድምፂ ትግራይ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ” በሚል አዲስ ስም የብሮድካስት ፈቃድ መውሰዱን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው፡፡
የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ቀደም ሲል “ድምፀ ወያነ” ይባል የነበረውንና በሕገ-ወጥ ይዘቶች ሳቢያ ፈቃዱ ተሰርዞበት የቆየውን ጣቢያ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ” ማእዶት ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ” በሚል አዲስ ስያሜ ፈቃድ አስወጥቶለት የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በድጋሚ የስያሜ ማሻሻያ በማድረግ ” ድምፂ ትግራይ ብሮድካስቲንግ አገልግሎት ” በሚል አዲስ ስም የብሮድካስት ፈቃድ መውሰዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።
ባለሥልጣኑ ጥቅምት 29 ቀን 2019 ዓ.ም እንደገለጸው፣ የክልሉ ባለአደራ አስተዳደር የፖለቲካና ሕዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ቀድሞ በወሰደው ስያሜ ላይ ማሻሻያ መደረጉን በደብዳቤ በማሳወቁና ፈቃዱ በዚሁ መሠረት እንዲስተካከልለት በመጠየቁ ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ በመቀበል የብሮድካስት አገልግሎት ፈቃዱን በአዲሱ ስያሜ አጽድቆ ሰጥቷል።
መረጃው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተገኘ ነው።
