EthiopiaNews

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለኤ ኤም ጂ ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ እና ለናይልብሪጅ ኢንቨስትመንት ባንክ ኃላ/የተ/የግ/ማ የኢንቨስትመንት ባንክነት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ባለስልጣኑ የሁለቱን አዳዲስ ኢንቨስትመንት ባንኮች ስምንት ተሿሚ እንደራሴዎች እና የአሥር ቦርድ አባላት ሹመትን አጽድቋል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዳግማዊት ሽፈራው ፈቃዱን ዛሬ በዋና መ/ ቤት በተዘጋጀ መርሃ ግብር ለ2ቱ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ባንክ አመራሮች በይፋ አስረክበዋል።

በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጭዎች ጠቅላላ ቁጥር ወደ 23 ሲደርስ የኢንቨስትመንት ባንኮች ቁጥር ወደ 11 አንድ ከፍ ብሏል።

ዋና ዳይሬክተሯ ፈቃድ ለተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ባንኮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ኢንቨስትመንት ባንኮቹ ደረጃውን የጠበቀ ሙያዊ አገልግሎት በመስጠት በገበያው ላይ ግልጽ እና ፍትሀዊ ግብይት እንዲሰፍን እንዲሁም ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልን በማረጋገጥ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስበዋል።