EthiopiaNews

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ116 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸውን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2ሺህ 86 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡
‎
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 9 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 664 ወንዶች፣ 387 ሴቶች እና 35 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 63 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።

‎ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡