EthiopiaNews

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።

አየር መንገዱ ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

አቶ አደም ፋራህ ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ቦርዱን ሲመሩ የነበሩትን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳን በመተካት ነው የተሾሙት።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ አደም ፋራህ የአየር መንገዱ አዲሱ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆናቸው የተሰማውን ከፍተኛ ደስታና አክብሮት ገልጿል።

አየር መንገዱ አክሎም አዲሱ ሊቀመንበር ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ቤተሰብ በደህና መጡ በማለት አቀባበል ያደረገ ሲሆን በቀጣይ የኃላፊነት ጊዜያቸው መልካምና የተሳካ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።