InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ፍላጎት ካላቸው በአንድ ስብሰባ ብቻ የዩክሬንን ጦርነት ማስቆም እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አስታውቀዋል።

ዛሬ በቻይና ሼንዘን ከተማ ከሚካሄደው የሶስትዮሽ ጉባኤ አስቀድሞ መግለጫ የሰጡት ዘለንስኪ አሜሪካና ቻይና በሞስኮ ላይ ማዕቀብ በመጣል ፑቲንን የማስቆም በቂ አቅም እንዳላቸው ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ያለ ዩክሬን ተሳትፎ ስለ ዩክሬን እንዲሁም ያለ አውሮፓ ተሳትፎ ስለ አውሮፓ ደህንነት ምንም ዓይነት ውሳኔ መወሰን እንደሌለበት ፕሬዝዳንቱ በጥብቅ አሳስበዋል።

በዛሬው ዕለት በበርሊን በሚካሄደው የአጋር ሀገራት ስብሰባ ላይ የአሜሪካ ተወካዮች ተገኝተው ስለ ቻይናው ውይይት ለዩክሬን ገለጻ እንደሚያደርጉና ለመከላከያና ለኃይል ዘርፎች አዲስ ድጋፍ እንደሚዘጋጅ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ ኮሚሽን ለዩክሬን እስከ 45 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ያቀረበውን ዕቅድ ዘለንስኪ በደስታ የተቀበሉት ሲሆን ፖርቹጋልም 50 ሚሊዮን ዶላር መለገሷ ተረጋግጧል።