የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በመዲናዋ ባለፉት አራት ወራት ከ1328 ለሚበልጡ ባለኃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
መ/ቤቱ በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባለሐብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነው ያስታወቀው።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ መ/ቤታቸው ባለፉት አራት ወራት 1328 አዲስ ፍቃድ ፣ 86 ለውጥ ፣ 250 የእድሳት አገልግሎት እና ለ21 የውጭ ዜጋ ቅጥር መስጠቱን እንዲሁም ከእነዚህ አገልግሎቶች 8.88 ሚሊዮን ብር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሯ ከ5.8 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ከ2 ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም የስራ ዕድል ባለፉት አራት ወራት መፈጠሩን ተናግረዋል።
ኮሚሽነሯ ለባለሐብቶቹ የኢንቨስትመንት አዋጁ የሚፈቅድላቸው የተለያዩ ማበረታቻዎችን ለጉሙሩክ ኮሚሽን እያቀረበ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
