InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ኢራን የሰላም ድርድሩን እያጓተተች ነው ሲሉ በመክሰስ ከአዲሱ ዓመት በኋላ በቴህራን ላይ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት ሊከፍቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ ካልደረሱ አዲስ ጥቃት ለማዘዝ መዘጋጀታቸውን እና የአሜሪካን የባህር ኃይል እገዳ ጥሰው የሚያልፉ የኢራን መርከቦችን እንደሚመቱ ዝተዋል።

ይህ የትራምፕ ማስጠንቀቂያ የተሰማው ኢራን የአሜሪካን እገዳ በመቃወም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በኩል የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ለማሳለፍ እየተዘጋጀች ነው የሚሉ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ ነው።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ሀገራቸው የነዳጅ ንግዷን ለመቀጠል መወሰኗን ገልጸው፣በመርከቦቻቸው ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በፋርስ ባህረ ሰላጤ የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በሳለፍነው ቅዳሜ ዕለት የኢራን አብዮታዊ ዘብ በባህሬን በሚገኙ የአሜሪካ የአየር መከላከያ ራዳሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ካስታወቀ በኋላ ውጥረቱ ይበልጥ መባባሱ ተመልክቷል።