በሊቢያ ቤንጋዚ ወደብ የነበረች አንድ የሩሲያ ነዳጅ ጫኝ መርከብ የድሮን ጥቃት ደረሰባትፎቶ)WEB
በሊቢያ ቤንጋዚ ወደብ የነበረች አንድ የሩሲያ ነዳጅ ጫኝ መርከብ የድሮን ጥቃት ደረሰባት።
መርከቧ ትላንት እሁድ ማለዳ አደጋው የደረሰባት ከሊቢያ ወደ ሩሲያ ለመመለስ ነዳጅና ሌሎች ቁሳቁሶች እየጫነች ባለችበት ወቅት ነው።
የምስራቃዊ ሊቢያ መንግስት የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ገልፆ መግለጫ ቢያወጣም ከሩሲያ ወገን በጥቃቱ ላይ የተባለ ነገር የለም።
በሊቢያ ያለው የመንግስታቱ ድርጅት ተልዕኮ ጥቃቱ እንዳስደነገጠው ገልፆ በጥቃቱ ላይ ገለልተኛና ነፃ ምርመራ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
ተመድ እንዳለው ሊቢያ የውጭ ባላንጣዎች የውጊያ ሜዳ ልትሆን አይገባም ብሏል።
