EthiopiaNews

ብሔራዊ ባንክ የ140 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ160 ብር ከ73 ሳንቲም ሸጠ።

ባንኩ ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

በዚሁ ጨረታ በተጫራቶች 160 ነጥብ 76 ሚሊየን ዶላር ፍላጎት መታየቱን ነው ባንኩ የገለፀው።

በዚህ ጨረታ ከተሳተፉት 32 ባንኮች ውስጥ 28ቱ አሸናፊ መሆናቸው ባንኩ ገልጿል።

ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረገው የ140 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ159 ብር ከ70 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።

መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።