7ኛው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት በቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸውን ዋና ዋና አቅጣጫዎች እንዲሁም በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ሥራዎችንና የተገኙ ውጤቶችን ያብራራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
