የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባለፉት 4 ወራት ወደ ውጪ ከተላከው ምርት 3 ነጥብ 95 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ በአራቱ ወራት 4 ነጥብ 29 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ ለማስገኘት ታቅዶ፣ 3 ነጥብ 95 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱንና ይህም የዕቅዱን 91 ነጥብ 9 በመቶ ማስመዝገቡን ገልጿል።
ይህም አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 3 ነጥብ 37 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር የ17 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው ሚኒስቴሩ የገለፀው።
