የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ያለአግባብ በኮሪደር ልማት ላይ የለቀቁ አልፎዝ ፕላዛ እና ሳሚ ህንፃ 800,000 ብር መቀጣታቸውን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣኑ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ኢምፔሪያል አካባቢ የሚገኘው አልፎዝ ፕላዛ እና “ሳሚ ህንፃ” ከፍተኛ የሽንት ቤት ፍሳሽ ወደ ተገነባው የኮሪደር መስመር በመልቀቅ አካባቢውን በመበከላቸው አስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት መቀጣታቸውን አስታውቋል፡፡
ቅጣቱ የከተማ አስተዳደሩ ባወጣው ደንብ ቁጥር 180/2017 (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ) መሰረት፣ ህግ በመተላለፋቸው እያንዳንዳቸው 4 መቶ ሺህ ብር በድምሩ 800 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
የተወሰደው እርምጃ የከተማዋን ውበት ለመጠበቅ እና የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የወጡ ደንቦችን ለማስከበር የተጀመረው ጥብቅ ቁጥጥር አካል መሆኑን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
መረጃው ከአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
