የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ታከናውናለች በተሰኘው እና ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ብሂራዊ ጉባኤ በየደረጃው የተጓዝንበትንና አሁን የደረስንበትን መንገድ መለስ ብዬ እንድቃኘው አድርጎኛል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ታከናውናለች በተሰኘው በዚህ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ በመገኘቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ነው ያሉት።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ሀገራችን በራሷ አቅም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች ያሉ ሲሆን እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ የተገኙ ድሎች ሳይሆኑ በመደመር መንፈስ ላይ ተመስርተው፣ ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው በጋራ በመቆም ነው፤ በሚል ጽኑ እምነት የተወሰዱ፣ በቆራጥ ውሳኔዎች የተገኙ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።
የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም፤ ይልቁንም ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ተከታታይ ትውልዶች የምንጥለው ጠንካራ መሠረት ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት።
ሀገርን መገንባት በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን የሁላችንም የጋራና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሆኑ፤ በዚህ ጽኑ እምነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መንፈስ ይዞ ወደፊት እንዲጓዝ የተቀበለውን ወረት አግዝፎ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያመራ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪያቸውን ያቀረቡት።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
