EthiopiaNews

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ጠንካራ ርዕይና አመርቂ አፈጻጸም እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ተናግረዋል።

ቻታም ሃውስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የምርምር ተቋም በለንደን ያዘጋጀውና በተከፋፈለ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ የኮፕ ጉባኤዎችን አስፈላጊነት ማጉላት በሚል ርዕስ በተካሄደው የአየር ንብረት ሳምንት የውይይት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ32 ተሰያሚ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ይህንን ያሉት።

ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ያላትን ጠንካራ ርዕይ እና አመርቂ አፈጻጸም ያነሱት ሚኒስትሩ በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በፖሊሲ ተደግፈው ተግባራዊ የተደረጉ አፈጻጸሞችን አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።

የኮፕ32 ተሰያሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት ጌዲዮን ጢሞቴዎ ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው የኮፕ32 ቀዳሚ ተግባራት፣በቱርክና አውስትራሊያ በጋራ ከሚዘጋጀው የኮፕ31 የተገኙ ውጤቶች በመነሳት፣ ቀጣይነትን ማረጋገጥ እንደሚሆን የጠቆሙ ሲሆን ይህ አካሄድም ከኢትዮጵያ በፊት የኮፕ ጉባኤዎችን ካዘጋጁት አገራት ጋር በቅንጅት በመስራት የጋራ ተግባራትን ማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የታደሙ ኃላፊዎች፣ ተቋማት፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ተግባራዊና አዲስ የፈጠራ መፍትሄዎችን በጋራ ለማዘጋጀት እንዲሠሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ጠንካራ አጋርነትን እንደሚያሳድጉና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ፈተናዎችን ለመፍታት፣ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ልማትን ለመደገፍ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን እንደሚያመነጩ አመልክተዋል።

ለመላው ዓለም የሚጠቅሙ መፍትሄዎችን ለማዘጋጀት ሀብታችንን፣ የጋራ እውቀታችንን እና የጋራ ቁርጠኝነታችንን ጠምረን መተግበር አለብን ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN