በፈረንሳይ የተከሰተው ከፍተኛ መጠን ያለው ሙቀት በትንሹ የ18 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ ተነገረ።
ከፊል አውሮፓን እየፈተነ ባለው በዚህ ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በፈረንሳይ ሕይወታቸው ካለፈው 18 ሰዎች መካከል ሁለቱ ሕፃናት መሆናቸው ሲነገር የህልፈታቸው ምክንያትም ወላጆቻቸው መኪና ውስጥ ትተዋቸው በመሄዳቸው ነው ተብሏል፡፡
ትላንትና በፈረንሳይ የነበረው ሙቀት ከ40 ድግሪ ሴልሺየስም ተሻግሮ 42 ድግሪ ሴልሺየስ አካባቢ መድረሱ የተነገረ ሲሆን ይህም በፈረንሳይ አንዳንድ ከተሞች ከዚህ በፊት የነበረውን አማካይ ሙቀት እጥፍ ሆኖ መመዝገቡ ነው የተመለከተው፡፡
ከፈረንጆቹ 1947 በኋላም የአሁኑ ሙቀት በፈረንሳይ ክብረ ወሰን ሆኖ መመዝገቡ የተነገረ ሲሆን በዚህም ምክንያት አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ጥቂቶቹ ደግሞ የሰዓት ለውጥ ማድረጋቸውን ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
