ተመድ በሆርሙዝ ሰርጥ መውጫ አጥተው የቆዩ 11 ሺህ ባህርተኞችን ማውጣት መጀመሩን አሳወቀ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓለምአቀፍ ማሪታይም ድርጅት በሆርሙዝ ሰርጥ መውጫ አጥተው የቆዩ 11 ሺህ ባህርተኞችን ማውጣት መጀመሩን አሳወቀ።
አሜሪካና ኢራን በቅርቡ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ነው ተመድ የኢራን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ላለፉት ሦስት ወራት ያህል በሆርሙዝ ሰርጥ መውጫ አጥተው የቆዩትን ባህርተኞች የማውጣት ስራውን የጀመረው፡፡
ባህርተኞቹን የማውጣቱ ስራው እየተከናወነ ያለው ደግሞ ሰርጡን ከሚያዋስኑት ኢራንና ኦማን እንዲሁም ከአሜሪካ እና የባህር ትራንስፖርት ኢንደስትሪዎች ጋር በመተባባር መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
አሜሪካና ኢራን የመግባቢያ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ሲነገር መውጫ ያጡትን ባህረተኞችም ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ የማውጣት ስራው ቀስ በቀስ እንደሚቀጥል ጠቅሶ የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
