EthiopiaNews

ሂዩውማን ራይትስ ዎች በምርጫ ቦርድ የታገደው ህወሓት በትግራይ ክልል ያወጣውን አዋጅ እንዲሰርዝ ጠየቀ::

ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩውማን ራይትስ ዎች፣ በምርጫ ቦርድ የታገደው  ህወሓት በትግራይ ክልል ያወጣውን የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትና የሃሳብ ነጻነትን የሚገድብ አዋጅ በአስቸኳይ እንዲሰርዝ ጠየቀ። 

ተቋሙ ባወጣው መግለጫ አዋጁ፣  ከፓርቲነት የታገደው ህውሃት  በፌዴራል መንግሥት የተሾሙትን የጊዜያዊ አስተደዳደር አመራሮች ካባረረ በኋላ የተጀመረውን መጠነ ሰፊ የግዳጅ ምልመላ ዘመቻ ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት ያለመ መሆኑን አመልክቷል።

ይህ ህዝባዊ ውይይት ሳይደረግበት የጸደቀ አዋጅ ዕድሜና ጤናቸው ለሚፈቅድላቸው ዜጎች ሁሉ ውትድርናን ግዴታ የሚያደርግ ነው ያለው የሰብአዊ መብት አራማጁ  የግዳጅ ምልመላውን በተቹ አካላት ላይ እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይደነግጋልም ብሏል።

ሂዩውማን ራይትስ ዎች አዋጁ በትግራይ ሰላምና አንድነት ላይ አደጋ መጣል በሚሉ ሰፊ ትርጓሜዎች ላይ እስከ ሞት ቅጣት የሚያደርሱ እና ለዳኝነት አስቸጋሪ የሆኑ ከባድ ቅጣቶችን አካቷል ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት የክልሉ ባለስልጣናት ህጻናትን ጨምሮ አዳዲስ ተዋጊዎችን ለመመልመል የቤት ለቤት የጅምላ አፈሳ እያካሄዱ ነው ያለ ሲሆን ከአፈሳው የሚያመልጡ ወጣቶች ወላጆችና ልጆች ጭምር በጸጥታ ኃይሎች ቅጣት እየተጣለባቸው ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት በርካታ ዜጎች አካባቢያቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ በመሆናቸው፣ የአፍሪካ ህብረት እና ዓለም አቀፍ አጋሮች የትግራይ ባለስልጣናት የግዳጅ ውትድርናውን እንዲያቆሙ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት እንዲያደርጉ ሲል ድርጅቱ አሳስቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews