የቴክኖሎጂ ኩባንያው ካስፐርስኪ በዋትስአፕ የሐሰት የንግድ ሰነዶችን በመጠቀም የሳይበር ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን አስታወቀ።
ኩባንያው በዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ እና የኮምፒውተሮችን ደህንነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል አዲስ የማጭበርበር በበርካታ ሀገራት ላይ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ገልጿል።
ጥቃቱ ዋትስአፕን በኮምፒውተር ላይ የሚጠቀሙ ሰራተኞችንና ነጋዴዎችን ያነጣጠረ ሲሆን፣ ኮምፒውተርን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርና መረጃ ለመስረቅ ያስችላል።
ማድረግ ያለብዎት:-
✔️ማንኛውንም ፋይል ከመክፈትዎ በፊት ለላኪው በስልክ ደውለው ትክክለኛነቱን ያረጋግጡ።
✔️በዋትስአፕ የሚላኩ መጨረሻቸው .vbs የሆኑ ፋይሎችን በፍጹም አይክፈቱ።
✔️ሁልጊዜ የጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር ይጠቀሙ። መረጃው ከኢንሳ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
