EthiopiaNews

ኢሰመኮ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ የተመለከቱ ህጎች እንዲወጡና የሚያስፈጽም አካል በህግ የሚሰየምበት ሁኔታ እንዲኖር ጥያቄ አቀረበ።

ኮሚሽኑ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ትናንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የ11 ወራት የሥራ ክንውን ሪፖርት ነው።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሀኑ አዴሎ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችንና ስደተኞችን በተመለከተ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ብሔራዊ ስትራቴጂዎች ተዘጋጅተው እየተሰራባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የሚከታተላቸው ራሱን የቻለ ተቋም እንዲኖር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።መረጃው ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews