EthiopiaNews

ኤም ቪ ጊቤ የተባለችው የኢትዮጵያ መርከብ ከሆርሙዝ ሰርጥ ወጥታ ወደ ጅቡቲ እየተመለሰች ነው ተባለ።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ኤም ቪ ጊቤ የተባለችው የኢትዮጵያ መርከብ ከእነጭነቷ ከሆርሙዝ ሰርጥ ወጥታ ወደ ጅቡቲ እየተመለሰች መሆኑን አስታወቀ።

ኩባንያው ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ቆመው ከነበሩ መርከቦች መካከል አንዷ የኢትዮጵያዋ የኤም ቪ ጊቤ መርከብ እንደነበረች አስታውሷል።

የኤም ቪ ጊቤ መርከብ ከእነጭነቷ ከሆርሙዝ ሰርጥ ወጥታ በአሁኑ ወቅት በኦማን ሰርጥ አካባቢ እንደምትገኝ እና የፊታችን ሰኔ 28 ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ወደ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስም ይጠበቃል ተብሏል።

የኤም ቪ ጊቤ መርከብ በ347 ዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሚያውለበልቡ መርከቦች መካከል አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

ኩባንያው በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ የነበረውን ከፍተኛ ውጥረትና ዕለታዊ ስጋት በጽናት ተቋቁማችሁ፣ ሀገራዊና ሙያዊ ክብራችሁን ያስጠበቃችሁ ጀግና መርከበኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።መረጃው ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews